You Are Here: Home > Press Releases > Press Release Viewer
        
 

Press Release (July 26, 2014)

 
   
 

Download in PDF Format


ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሪጅንን በመወከል የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች


ኢትዮጵያ የአፍሪካ (ምስራቅ አፍሪካ) ሪጅን አንድን በመወከል የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆና ጄኔቭ ስዊዘርላንድ በሚገኘው የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ካውንስል ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ መመረጧ ታውቋል።

አቶ ፈጠነ ተሾመ የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ የአፍሪካ አህጉር ብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ ድርጅቶችን በመወከል ከተመረጡት ሰባት አባላት መካከል አንዱ ሆነው በሥራ አስፈፃሚ አባልነት የተመረጡ መሆኑን ታውቋል።

የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት የድርጅቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካል ሲሆን፣ ሀላፊነቱም የኮንግረሱን ውሳኔዎችን መተግበር፣ ፕሮግራሞችን ማስተባበር፣ በጀት ነክ ጉዳዮችን መመርመር፣ በዐለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት መዋቅራዊ አደረጃጀት መሰረት በሪጅናል አሶሴሽን ጉዳዮች ላይ የተሰጡትን ተግባራት ማከናወን፣ ቴክኒካዊ እገዛዎችን መስጠት እንዲሁም በአየር ሁኔታ፣ በአየር ጠባይና በውሃ ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ሁኔታዎች ላይ ርምጃዎች መውሰድን ያካትታል።

የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ከ37 የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂና ኃይድሮሎጂ አገልግሎቶች በተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች የተዋቀረ ሲሆን ውክልናቸውም ስድስቱ ደግሞ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ሪጅናል አሶሴሽን ፕሬዝደንቶች መሆናቸውን ታውቋል።



ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


Back to List


 
   
   

RSS Subscribe for Bulletins